Friday, September 2, 2011

የስደተኛው ህጻን ጸሎት

ሰንዱቅ አልጠይቅ ብር የተሞላ
ሱሪም አልፈልግ ከሀር የተሰራ
ይቅርብኝ 'ልልታችሁ ይቀመጥ ለኋላ
ግና...
ስጡኝ መሬት 'ትብቴን ምቀብርበት
ስጡኝ አገር እንድኖር ሣላፍር

እኔም አይደለሁ...

የማር የወለላ የጥፍጥና ገንቦ ተነግሮኝ መሆንሽ
አንዳች ጭምብል ሳይኖር
ማር እቆርጥ ብዬ ብጠጋ ከቀፎሽ
እባጭ ፊቴን ሞልቶት ሸሸሁ ከሠፈርሽ::
አንዴ ከመቅመሴ ከወለላ ማርሽ
ሰው ፊት እንዳልቀርብ
ከውስጥ የመሠጉ ነድፈውኝ ንቦችሽ::