Saturday, January 28, 2012

ሲቀና ይውላል

ነግረውኝ ነበር ፍቅር እንዳይቀና
የሰውን እንዳይመኝ እንዲሰጥ ለሌላ
እኔ ግን ፍቅርን መቼ እንዲህ አገኘሁት
አጥር ሰርቶ ቀጥሮ ያለውን ላለማጣት
ሊወስድ የመጣውን ጠላት ብሎ ጠርቶት
ሲከለክል አይቼ ፍቅርን ታዘብኩት

No comments: