Saturday, January 28, 2012

ያልተማረው

ፍቅርን ለሸቀጠ
በጥቅም ለለወጠ
ይሉኝታን አልፎ ተራምዶ...
እሱን የወደደውን
በርሱ የተጠላውን
አሳልፎ ለሚሰጥ ለማይራራው ልቡ
አክስሮ ማትረፍን ለተለማመደው
መሞቱን ብሰማ መኖሩን ሳላውቀው
እምባም አልወርድ አለኝ ልቤን አልደነቀው
መኖርን ሳይማር መሞትን ከየት አወቀው?

No comments: