እኔው በወለድኩኝ እኔው ባ'ማጥኩት
ከዳር ቆሞ ሲያይ ፈዞ ሲመለከት
የልቡ ሸፍጥ ገብቶኝ የውስጡን ተረድቼ
ሊያደርስ ያለውን ጥፋት ከሩቁ አይቼ
ለመደበቂያ የሚሆን ብፈልግም ቦታ
የጥርጣርዬ ትንሿ ጠብታ
ስላሣየችኝ የፊቱን አጥርታ
ሁሉን በየተራ አስቀድሜ ስቀብር
የወላጅነት ቅስሜ በቶሎ ሲሰበር
ስላንቀጠቀጠኝ ነገሩን ሣስበው
ከኔ ከሚርቁ ጠላት ከሚወስዳቸው
አምጬ እንደወለድኩ እኔው እንዳመጣኋቸው
ከወጡበት ሆድ እኔው መለስኳቸው።
(For those who grew up listening the folklore that
cat prefers eating her kittens to being watched by
human while giving birth...)
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment